HR 2003 is re-scheduled for mark-up for July 18th. Have you called, emailed, or faxed your representative yet? If not, what are you waiting for? Pick up your phone and do it right now. This is the least you can do to help the end of dictatorship and the beginning of democracy in your country. You have made a call already? That is good. But how about your family, roommates, classmates, next door neighbors, colleagues at work, people at your mosque or church? Make sure to spread the word and get as many people as possible to contact their representative. Don’t under estimate your contribution. You can really make a difference.Let us join hands and do this right now.
Sunday, July 15, 2007
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
1 comment:
ዶክትር ማሩ፣
በዲያስፖራ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ ተሳትፎ አስመልክተዉ ያቀረቡት አስተያየትዎን በጽሞና አንብቢያለሁ። በኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ መስመር ይዞ አለመንቀሳቀሱ ያስከተለዉን ቀዉስና መከፋፈል ለትግሉ እንደማይጠቅም እርስዎ እንደገለጹት የሁላችንም ስጋት ሆኑአል። በእኔ አመለካከት ችግሩን የምንጠይቅ ዜጎች እየተበራከትን ሲሆን መፍትሄዉን ለማቅረብ የምጥር ግን ቁጥራችን እየመነመነ ይገኛል።
ዶር፡ በመጀመሪያ እርስዎ በምርምርና በጽናት ላይ ተመርኩዘው ያቀረቡትን ጽሁፍ በዚች መናኛ ደብዳቤዬ መልስ ለመስጠት በመድፈሬ በተለመደዉ ኢትዮጵያዊ ባህላችን ይቅርታ እጠይቃለሁ።
ለእርስዎ ግልጽ ቢሆንም እንዳይረሱት ላስታዉስዎት የምፈልገዉ ነገር ቢኖር አንድ ሃገር የምትገነባዉ በተማርን ባዮች ብቻ አለመሆኑን እንዲረዱት ያስፈልጋል። የተማሩና የተመራመሩ ምሁራን ለሚያቀርቡት አስተያየት መነሻ/ማረጋገጫ ይዘዉ መቅረብ አንባቢን ለማሳመንና ተሰሚነትን ለማትረፍ ይጠቅማቸዋል። በዚህ ላይ ከእርስዎ ጽሁፍ የቀረበ ባለመኖሩ ራስዎን ዝቅ አድርገው ወደአልተማረዉ ክፍል እንዳይመደቡ ጥንቃቄ ቢያደርጉ ይመረጣል።
ዶር ማሩ ፡ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ችግሩን አዉስተዉ መፍትሄ ሃሳብ ባለማቅረብዎ የጽሁፍዎ መልእክት ለአንባቢያን ግልጽ አይደለም። ከዚህ በላይ የምለው አይኖርም።
ዶር የከረንት አፌርስ ዲስከሽን ፎረምን አስመልክተው ያቀረቡት አስተያየት አፍራሽ ሆኖ ተመልክቸዋለሁ። የዚህ ፎረም ተሳታፊዎች፣ ቀደም ሲል በተለያዩ ምክንያቶች ማለትም፣ በቀይ ሽብር እንዲሁም የወያኔ የዘረኛ አገዛዝ በዘራዉ መርዝ እየደበዘዝ የሄደዉን የኢትዮፕያዊነት ወኔ፣ አልነካም ባይነትና ከራሴ በፊት ለእናት ሃገሬ የሚለዉን ሞራል ለወጣቱ ትዉልድ ለማላበስ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገጙ ጀግና ኢትዮጵያዊያን ናቸዉ። በፖለቲካ መስኩም ቢሆን ዓለም አቀፉን የቅንጂት አመራሩና የአርበኞች ግንባርን በተቻላቸው ሁሉ እየደገፉ ይገኛሉ። ከዚያም ሰፋባለመልኩ የኢትዮጵያን ዉስብስብ ችግሮች በዉይይት ለመፍታት የተጀመረዉን ዉጥን አዔፍዲን ይደግፋሉ። ታዲያ ምኑነዉ የሂህ ፎረም ስህተት።
ዶር ማሩ ምናልባት አንዳንድ የፎረሙ አባላት ካላቸው የጠለቀ ኢትዮጵያዊነት ፍቅር የተነሳ ሃሳቦችን በቁጣ ሊያስተናግዱ ይችል ይሆናል። ይህ ደግሞ ከተመክሮ ማነስና ከብስጭት የሚመነጭ ስለሆነ እንድናንተ ዓይነቱ ብቃቱና ልምዱ ያላችሁ ወገኖች ምክራችሁን ብትለግሱ የሚታረምና በቀላሉ የሚስተካከል ይመስለኛል።
ድር ማሩ ያሳዘነኝ ነጥብ ቢኖር ወያኔዎች በክብር የሚስተናገዱበት፡ ኢትዮጵያን የገደለና ለጠላት አሳልፎ የሰጠው ተከብሮ፤ ክቡር ህይዎታቸዉን ለሰላምና ለዴሞክራሲ አሳልፈዉ ከሰጡት ጀግና መሪዎቻችን ጋር እኩል ክብር እየተሰጠ ፡የኢትዮጵያ ኩሩነት ባህል እየተበረዘ አጎብዳጅነት እየተሰበከበት ያሉተን ፎረሞች ከመተቸት ተቆጥበዉ ከፎረሞች ሁሉ አንጋፋ በሆነዉ በከረንት አፌርስ ዲስከሽን ፎረም ላይ የጭቃ ጅራፍ ለመለጠፍ ማሰቡ ለትግሉ የሚጠቅም አይመስለኝም። ለዎደፊቱም መዳበር ያለበት የዚህ ዓይነት መድረኮች መሆን አለበት። ወጣቱን የሚያሰባስብ አልገዛም ባይነትን የሚሰብክ፣ አድባይነትንና አጎብዳጅነትን የሚያዎግዝ መድረክ ለትግሉ ጠቃሚ ይመስለናል።
ዶር ማሩ እንደ እኔ እምነት ትግሉን ያዳከመዉና ያጛተተዉ የከረንት አፌርስ ታዳሚዎች ሳይሆኑ፣ ተምረናል የሚሉና ሃሳብ ከደጋፊዎች ለመቀበል ዝግጁ ያልሆኑ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል ባዮች ይመስለኛል። በዚህ ዙሪያ ብቃቱ ስላለዎት የሚጠበቅብዎትን ድርሻ ቢዎጡና ለዉይይት መድረኩን ቢፈጥሩ ሃስቤን እሰነዝራለሁ።
ኦሪዮን
Post a Comment